Posts

ቄስ ቀፀላጊዮርጊስ ደስታ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፅ/ቤት ፤አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር የሰ/መ/ቁጥር 218309

ቄስ ቀፀላጊዮርጊስ ደስታ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፅ/ቤት ፤አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ቤቶች አስተዳደር የሰ/መ/ቁጥር 218309 : በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጀመረው የሁከት ክርክር የሰበር አመልካች ከሣሽ፣ የሰበር አንደኛ ተጠሪ ተከሣሽ፣የሰበር ሁለተኛ ተጠሪ ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል፡፡ አመልካች ግንቦት 2ቀን 2013ዓ/ም በተፃፈ ክሣቸው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 648 የሚታወቀው ቤት የግል ቤታቸው መሆኑን፤ የቤት ቁጥር 649 ደግሞ የአስተዳደሩ ሆኖ አመልካች የግል ቤታቸው ስለ%...
10 መሰረታዊ የውል አተረጓጎም ደንቦች *** በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ እና የህግ አማካሪ) *** ውል ቅኔ መሆን የለበትም። በተቻለ መጠን ለሁሉም ተዋዋይ  ወገን እንዲሁም ለሶስተኛ ወገኖች ጭምር ግልፅ በሆነ መንገድ መደረግ አለበት ። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በተለያየ መንገድ የሚደረጉ ውሎች ግልፅነት የጎደላቸው ይሆኑና የግጭት ና ያለሙግባባት  መንስኤ ሆነው ለትርጉም አስማሚ ወይም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ይህ ሲሆን ፍርድ ቤቶች ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ መሰረታዊ የሆኑ የውል አተረጓጎም ደንቦች አሉ። እነሱን እጠር አርገን ከተያያዥ የሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉሞች ጋር  እንመልከት: የውል አተረጓጎም መሰረታዊ ደንቦች 1. ውሉ ግልፅ ከሆነ ምንም አይነት ትርጉም አያስፈልግም። ( If the contract is clear no need of interpretation ) /፩/ 2.  የውሉ ትርጉም ውጤት መገኘት ያለበት ከራሱ ከውሉ እንጂ ፣ ውሉ ወይም ግዴታው ከትርጉሙ ሂደት መመንጨት የለበትም። / The interpretation of the contract must come from the contract not the contract from the interpretation./  በሌላ አማርኛ ፍርድ ቤት ውልን በመተርጎም ስም ያልነበረ ውል ወይም ግዴታ ሊፈጥርና ሊሰራ አይችልም። 3. የቅን ልቦና አተረጓጎን ደንብ (1732)  :- ማንም ሰው የራሱን መብት በአግባቡ ከመጠቀም አልፎ በሌላው ተዋዋይ ላይ አላስፈላጊ ጉዳት የማድረስ ፍላጎት የለውም የሚል አወንታዊ  መነሻ ሃሳብ ( positive premise) አለ። ከዚህ ተቃራኒ የሄነ ሃስብ ይዞ ከቅን ልቦና በተቃራኒ ጉዳት ለማድረስ ያለው ተዋዋይ ወገን ካለ ህግ በመርህ ደረጃ ጥበቃ ያደርግለታል። /፪/ 4. በተገቢው መንገድ ያልተብራሩ ሃሳቦችን አተ

ተጠሪ

 ተጠሪ *         ዳንኤል ፍቃዱ / የህግ አማካሪና ጠበቃ/ * አንድ ተቋም ለአንድ ሌላ ተቋም ወይም ግለሰብ ተጠሪ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? ምን መብት ምን ግዴታስ በተጠሪው ላይ ይፈጥራል? በጠሪው ( ይጠራልህ በተባለው)ግለሰብ ወይም ተቋም ላይስ?  ከህገ መንግስቱ አንስቶ መመሪያ ድረስ ያሉ ህጎች ላይ ይህች ቀላል እምትመስል ቃል በየቦታው ተዱላ እንመለከታታለን ። በእንግሊዝኛው በተለዋዋጭ Accountable ወይም Responsible በሚል ተገልፃ እናገናታለን።  እውቁ የህግ መዝገበ ቃላት Blacks law Dictionaryንም ስንመለከት ቃላቱ በተለዋዋጭ / interchangeably/ አገልግሎት ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ ሲያጠይቅ: Accountable = Responsible በሚል ይተረጉመዋል። ስለዚህ ሃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ መልስ ሰጪነት ፣ ወዘተ ተብሎ ሊተረጎም ይችል ይሆናል። ለምሳሌ ያህል ፩/  የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 49 (3) ላይ " የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌደራሉ መንግስት ይሆናል። " ይላል። ምን ማለት ይሆን ?ሰበር በሠ/መ/ቁጥር 34665 ቅፅ 10 ላይ  " የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ስራ የመከታተልና በበላይነት የመቆጣጠር ስልጣን ያለው እንደመሆኑ መጠን የስራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ቤቶችን የሚመለከት ጉዳይ ለአዲስ አበባ ስራና ከተማ ልማት ቢሮ እንዲያስተላልፍ በተሰጠው ትዕዛዝ ( ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደብዳቤ ባስተላለፉት ) መሰረት ስራውና ሰራተኞችን ለቢሮው አስተላልፏል ። "  ይለናል ይህ ማለት እንግዲህ  የከተማ መስተዳድሩ በሚያወጣቸው ህጎች እና በሚወስናቸው ውሳኔዎች ሁሉ የፌደራሉን ይሁንታ ማግኘት አለበት ማለት ነው? ፌደራሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

QUESTIONING JURISDICTION OF OROMIA COURTS OVER CRIMES COMMITTED IN ADDIS ABABA

  FEBRUARY 7, 2021   ETHIOPIAN LAW BY DANIEL FIKADU   LEAVE A COMMENT   EDIT Draft Criminal Procedure and Evidence Code, Article 25 (3) A Draft Criminal Procedure and Evidence Code (Draft Code) intended to replace the 1961 Criminal Procedure Code has been submitted to the House of Peoples’ Representatives (HoPR) for its approval and promulgation. One of the matters the Draft Code regulates relates to the criminal jurisdiction of courts over crimes under the 2004 Criminal Code. This article examines Article 25 (3) of the Draft Code that empowers Courts of State of Oromia to exercise jurisdiction over some criminal cases in Addis Ababa. When seen in the light of the Constitutional division of power between the Federal Government and the States, this provision is constitutionally dubious and pragmatically flawed. Thus, the HPR needs to consider its omission from the final version of the Draft Code. Jurisdiction of Courts of the State of Oromia over Crimes Committed in Addis Ababa under th

የአጣሪ ዳኝነት ሚና በአስተዳደር ህግ

Image
  Ethiopian law by Daniel Fikadu Search SKIP TO CONTENT የአጣሪ ዳኝነት ምንነት እና ህገ መንግስታዊ ፋይዳውየአጣሪ ዳኝነት (Judicial Review) ትርጓሜ ከህገ መንግስት ወይም ከአስተዳደር ህግ አንጻር ሊቃኝ ይችላል፡፡ በህገ መንግስታዊነት ማዕቀፍ አጣሪ ዳኝነት ማለት በህግ አውጭው የሚወጡ ህጐች ህገ መንግስታዊ ባለመሆናቸው በመደበኛ ፍ/ቤት፣ በህገ መንግስታዊ ፍ/ቤት ወይም በሌላ ራሱን የቻለ ተቋም አማካይነት የሚሻሩበት ስርዓት ነው፡፡a በአስተዳደር ህግ ውስጥ አጣሪ ዳኝነት ማለት በህግ አስፈፃሚው ወይም በአስተዳደር መ/ቤቶች የሚወሰዱ ውሳኔዎች፣ የሚፈጸሙ ድርጊቶች እና በውክልና የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ህጋዊነት በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚጣራበት ስርዓት ነው፡፡b ምንም እንኳን በህገ መንግስታዊነት እና በህጋዊነት መካከል ጥርት ያለ መለያ መስመር ማበጀት አዳጋች ቢሆንም የዚህ መጽሐፍ በተለይም የዚህ ምዕራፍ ወሰን ህገ መንግስታዊ አጣሪ ዳኝነትን አያካትትም፡፡የአጣሪ ዳኝነትን ፅንሰ ሀሳብ በሚገባ ለመረዳት እንዲያስችለን በመስኩ ምሁራን የተሰጡ ሁለት ትርጓሜዎችን እንጠቅሳለን፡፡ በእንግሊዝ አጣሪ ዳኝነት ማለት በህግ ስልጣን የተሰጣቸው አካላት ስልጣናቸውን በመገልገል የሚፈጽሙት ድርጊት ወይም አልድርጊት (inaction) በከፍተኛው ፍርድ ቤት የሚጣራበት ስርዓት ነው፡፡Judicial review can be defined as the procedure through which the High Court supervises the public law actions and inactions of public authorities and other bodies that are exercising statutory powers, performing public duties, and/

ተወካይ የወካዩን እማይንቀሳቀስ ንብረት አስይዞ መበደር ስልጣን .... የሠ.መ.ቁ. 17320 / ቅፅ 5 / ላይ እና በመዝገቡ ላይ በኢትዮጵያ ጠበቆች የህግ መፅሄት መግዌ 5 ቁ.2 ላይ በተሰጠው ትችት ላይ የተሰጠ የትችት ትችት .....

ዳንኤል ፍቃዱ / በማንኛውም ፍ.ቤት ጠበቃ / 0913158507/ .... የሰበር ሰሚው ውሳኔ ባጭሩ ተከራካሪዎች ከታች ፍ.ቤት ጀምሮ ሲከራከሩ የነበሩበት በቤት ላይ የተሰጡ 2 የተለያዩ  ልዩ ውክልናዎች  ሲሆን አንደኛው ውክልና ህጋዊነቱ አልተካደም ሁለተኛው ውክልና ግን የተጭበረበረ ስለመሆኑ ክርክር ቀርቦበታል / በወንጀል ህግ ቁ. 358(1) እሚያስጠይቅ ድርጊት ነው ~ በወንጀል ክስ ስለመቅረቡ የፓሊስ ምርመራ መዝገብ እንደነበር ከመዝገቡ መረዳት ይቻላል /  አከራካሪው ድርጊት ተወካይ የተጭበረበረውን ውክልና ተጠቅመው የወከሉዋቸውን ባልና ሚስት / የተጭበረበረ በተባለው ሁለተኛው ውክልና ላይ ተወካዮች ሁለቱ ሳይሆኑ አንዱ ብቻ ነው/ ንብረት አስይዘው ከባንክ ብድር ተበድረው ለግላቸው ተጠቅመውበታል ፤ ባንኩም ይህን የተጭበረበረ ሰነድ ሳያጣራ አበድሯል፣ በተጨማሪም "ሁለቱም " ውክልናዎች የመሸጥ የመለወጥ እና የማስተዳደርን ስልጣን ለተወካይ ይሰጣሉ እንጂ አስይዞ የመበደር ስልጣን አይሰጡትም የሚሉ ሲሆኑ ። ጉዳዩን የተመለከቱት የመጀመሪያው እና ከፍተኛው ፍ.ቤቶች ባንኩ የወካዮችን ቤት በመያዣነት በመያዝ ብድር የሰጠው በአግባቡ አይደለም በማለት የመያዣ ውሉን ፈራሽ በማድረግ የባለቤትነት ሰነዱን ለወካዮች ይመልስ ሲሉ ወስነዋል። ሰበር ሰሚው ይህን ውሳኔ በመቀልበስ  1. ሁለተኛው ውክልና የተጭበረበረ ነው የሚለውን ብቻ በመመርመር የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። 2. ሊታይ እሚገባው ሁለተኛው ውል ሳይሆን የመጀመሪያ /ህጋዊው/ ውል ነው ምክንያቱም እሱም ፀንቶ ባለበት ነው የማስያዣ ውሉ የተደረገው / ምንም እንኳን ባንኩ ጋር የተደረገው የመያዣ ውል በ2ተኛው የተጭበረበረ ውል ቢሆንም / 3. የመጀመሪያ ውል አስይዞ የመበደር ስልጣን

የቤት ውሰጥ ሰራተኞች ህግ ??? በዳንኤል ፍቃዱ(ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)

Image
  የአሰሪና ሰራተኛ ህጉ አዋጅ ቁጥር1156/2011 በአኝቀፅ 3 ስር የህጉን ተፈፃሚነት ወሰን በሚደነግግበት ወቅት በግለፅ ካገለላቸው የቅጥር ግንኙነቶች ውሰጥ . የመንግስት ሰራተኞች(አንቀፅ 3/2/ሠ/ የሠበር መ.ቁ. 14414 ቅፅ 2 ይመልከቱ ) . የስራ መሪዎች ( አንቀፅ 3/2/ሐ/የሠበር መ.ቁ. 84661 ቅፅ 15 ፣የሠበር መ.ቁ. 92466 ቅፅ 15 ፣ የሠበር መ.ቁ. 11969 ቅፅ 20 ፣ እና ሌሎችንም የሰበር ውሳኔዎችን መመልከት ይቻላል) . የቤት ውሰጥ ሰራተኞች (አንቀፅ 3/2/መ/) ወዘተ…ሲገኙ በግልፅ ሳይሆን በቅድመ ሁኔታ የሚገለሉ የቅጥር ግንኙነቶችንም አስቀምጧል፡፡(አንቀፅ 3/3/)በዚህ አንቀፅ ላይ ህጉ አንዳንድ ለወደፊቱ ሊደረጉ የሚችሉ ነገሮችን ያስቀምጥናእነዛ ነገሮች ተሟልተው ሲገኙበተጠቀሱት የቅጥር ግንኙነቶች ላይ አዋጁ ተፈፃሚነት አይኖረውም ማለት ነው፡፡እነዛ ቅድመሁኔታዎች እሰካልተሟሉ ወይም እሰካልተፈፀሙ ድረስ ግን እነዚህ የቅጥር ግንኙነቶች የሚገዙት በአዋጁ መሰረት መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ገንኙነቶች ሁለት ሲሆኑ 1.በውጭ ኤምባሲዎች እና አለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሰሩ ሰራተኞች ( አንቀፅ 3/3/ሀ/) የሠበር መ.ቁ. 117390 ቅፅ 19፣ የሠበር መ.ቁ. 98541 ቅፅ 17 ይመለከቱ) 2.የሃይማኖት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሰራተኞች (አንቀፅ 3/3/ለ/) የሠበር መ.ቁ. 67996 ቅፅ 13፣የሠበር መ.ቁ. 50923 ቅፅ 9 ፣ የሠበር መ.ቁ. 98771 ቅፅ 20 ይመልከቱ) ለመነሻ ያክል የህን ካልኩ ለዛሬ የቤት ውሰጥ ሰራተኞችን ጉዳይ ላይ ትንሽ ልጨምር፤ የቤት ውሰጥ ሰራተኞች የሚባሉት በዋናነት የጓዳ ስራን የሚሰሩ፣ የሚያፀዱ ፣ምግብ የሚያዘጋጁ፣ ዘበኞችን እና አትክልተኞችን መጥቀስ ይቻላል፡፡እንደስራው ሁኔታ ሌሎችም ስ

በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የሚቀርብ ክስን ማየት ስልጣን ያለው ማነው? በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)

      በወታደራዊ አካሉ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ፣ የሃገር ክህደት ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ከፍተኛ መኮንኖች ላይ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የምርመራ መዝገብ መከፈቱን ተከትሎ ፣ እነዴት ወታደር በመደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ይታያል በሚል ስልጣን ጥያቄ እና በፍትህ ስርአቱ ላይ ትችት ሲሰነዘር ተመልክተናል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ ጠቅለል ባለ መልኩ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የሚቀርብ ክስን ማየት ስልጣን ያለው ማነው? የሚለውን ለመዳሰስ ተሞክሯል::       ፍርድ ቤቶች በህግ የሚቋቋሙ እንደመሆናቸው የዳኝነት ስልጣናቸው ከህግ ይመነጫል፡፡ በአንድ ፍርድ ቤት የቀረበ ጉዳይ የክስ ምክንያት አለው ብሎ ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሹ የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ህግ ይፈቅድለታል ወይ? የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት አወንታዊ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡       ከዚህ እንግዲ መረዳት የሚቻለው የማንኛውም ፍርድ ቤት ጉዳይን ተመልክቶ የመውሰን ስልጣን በህግ ተወስኖ የተሰጠ ወይም የሚሰጥ መሆኑን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ህግ ፍርድ ቤቶች ተፈጥሯዊ ስልጣን (Natural/inherent power) በህግ በሚታዩ ጉዳዮች (Justiciable matters) ላይ የላቸውም የሚለው ሃሳብ አከራካሪነቱ እንዳለ ቢሆንም በዙ ባለሙያዎች የሚስማሙበት ነው፡፡( በጉዳዩ ላይ ከዚህ ቀደም በቀድሞ ገፃች  https://m.facebook.com/groups/1607340246185508/?ref=bookmarks  ወይምhttps://m.facebook.com/Ethiopian-law-by-Daniel-Fikadu-law-office-510394779106487/?ref=bookmarks የፃፍከት ሰፋ ያለ ፅሁፍ ስላለ ፈልጋችሁ ተመልከቱት)ወታ