የቤት ውሰጥ ሰራተኞች ህግ ??? በዳንኤል ፍቃዱ(ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)

 

የአሰሪና ሰራተኛ ህጉ አዋጅ ቁጥር1156/2011 በአኝቀፅ 3 ስር የህጉን ተፈፃሚነት ወሰን በሚደነግግበት ወቅት በግለፅ ካገለላቸው የቅጥር ግንኙነቶች ውሰጥ
. የመንግስት ሰራተኞች(አንቀፅ 3/2/ሠ/ የሠበር መ.ቁ. 14414 ቅፅ 2 ይመልከቱ )
. የስራ መሪዎች ( አንቀፅ 3/2/ሐ/የሠበር መ.ቁ. 84661 ቅፅ 15 ፣የሠበር መ.ቁ. 92466 ቅፅ 15 ፣ የሠበር መ.ቁ. 11969 ቅፅ 20 ፣ እና ሌሎችንም የሰበር ውሳኔዎችን መመልከት ይቻላል)
. የቤት ውሰጥ ሰራተኞች (አንቀፅ 3/2/መ/) ወዘተ…ሲገኙ
በግልፅ ሳይሆን በቅድመ ሁኔታ የሚገለሉ የቅጥር ግንኙነቶችንም አስቀምጧል፡፡(አንቀፅ 3/3/)በዚህ አንቀፅ ላይ ህጉ አንዳንድ ለወደፊቱ ሊደረጉ የሚችሉ ነገሮችን ያስቀምጥናእነዛ ነገሮች ተሟልተው ሲገኙበተጠቀሱት የቅጥር ግንኙነቶች ላይ አዋጁ ተፈፃሚነት አይኖረውም ማለት ነው፡፡እነዛ ቅድመሁኔታዎች እሰካልተሟሉ ወይም እሰካልተፈፀሙ ድረስ ግን እነዚህ የቅጥር ግንኙነቶች የሚገዙት በአዋጁ መሰረት መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ገንኙነቶች ሁለት ሲሆኑ
1.በውጭ ኤምባሲዎች እና አለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሰሩ ሰራተኞች ( አንቀፅ 3/3/ሀ/) የሠበር መ.ቁ. 117390 ቅፅ 19፣ የሠበር መ.ቁ. 98541 ቅፅ 17 ይመለከቱ)
2.የሃይማኖት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሰራተኞች (አንቀፅ 3/3/ለ/) የሠበር መ.ቁ. 67996 ቅፅ 13፣የሠበር መ.ቁ. 50923 ቅፅ 9 ፣ የሠበር መ.ቁ. 98771 ቅፅ 20 ይመልከቱ)
ለመነሻ ያክል የህን ካልኩ ለዛሬ የቤት ውሰጥ ሰራተኞችን ጉዳይ ላይ ትንሽ ልጨምር፤ የቤት ውሰጥ ሰራተኞች የሚባሉት በዋናነት የጓዳ ስራን የሚሰሩ፣ የሚያፀዱ ፣ምግብ የሚያዘጋጁ፣ ዘበኞችን እና አትክልተኞችን መጥቀስ ይቻላል፡፡እንደስራው ሁኔታ ሌሎችም ስራዎች አዚህ ውሰጥ ሊካተቱ እሚችሉበት ሁኔታ በመኖሩ ዝርዝሩ አጠቃላይ አደለም፡፡ በተቃራኒውም አነዚህም እራሱ የቤት ሰራተኛ እንዲባሉ በአሰሪው ቤት ወይም ለአሰሪው የግል እና የቤተሰብ ፍጆታ መስራት አለባቸው፡፡እነዚህ ሰራተኞች አገልግሎታቸውን የሚሰጡት ለትርፍ ለተሰማራ አሰሪ ከሆነ የቅጥር ግንኙነቱ የሚመራው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ይሆናል ማለት ነው፡፡
አዋጅ ቁ 377/1996 ባሻሻለው አዋጅ ቁ 1156/2011 የቤት ውስጥ ሰራተኞችን “የግል አገልግሎት ቅጥር /employees of private/personal service” በሚል ጠቅለል ያለ ትርጓሜ ለመስጠት ሞክሯል።(አንቀፅ 2/16/)
በቱጨማሪም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ደንብ እንደሚያወጣበት ደንጓል።( አንቀፅ 3/3/ሐ)
ሃሰቤን እንዲያብራራልኝ አንድ ቆየት ያለ የሰማሁትን ጉዳይ ላንሳ አና ለመወያያነት ልተወው፤ ወ/ት የሻረግ እመት ትረፍነሽ ሆቴል ውስጥ በምግብ አብሳይነት ተቀጥረው በሚያገኙዋት 3500.00 ብር ህይወታቸውን እየመሩ በነበረበት ጊዜ ያለባቸውን የኑሮ ጫና አሰሪቸው ተመልክተው ባጋጣሚውም ቤታቸው የቤት ሰራተኛቸውን ካሰናበቱ ቀናት እየተቆጠሩ በመሆኑ የሻረግን የቤት ኪራይም የምግብም አያለች ከምትሰቃይ ከሳቸው ጋር እየኖረች ከሆቴሉ ስራ በመለስ የቤቱንም ስራ እንድታግዛቸው በደሞዝዋም ላይ ተጨማሪ ብር 500.00 ጨምረው ሊከፍልዋት ተሰማሙና በስምምነታቸው መሰረት የሻረግ እመት ትርፍነሽ ቤት ገብታ ሁለቱንም ስራዎች ለ1 ዓመት ያክል ባግባቡ ስታከናውን ቆይታ በሆቴል ሰራተኛ ብቻ በነበረችበት ወቅት ይሰጣት እንደነበረው ሁሉ አመታዊ የደመወዝ ጭማሪዋን ብትጠይቅም ቀጣሪዋ ጭማሪውን ለማድረግ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው በተነሳ አለመግባባት ከቤትም ከስራዋም ተሰናበተች፡፡
ወ/ት የሻረግ እርሶ ቢሮ መጥታ ይህን ጉዳይ ብታጫውቶት የሚከተሉት ጥያቄዋች ባአይምሮዋ መከሰታቸው አይቀሬ ነው፡-

  1. የወ/ት የሻረግ ጉዳይ በአሰሪና ሰራተኛ ህጉ መሰረት ነው ወይስ በፍታብሄር ህጉ ሰለቤት ሰራተኞች በተደነገጉ አናቅፅት አቤቱታዋን የሚያዘጋጁላት?
    2.ምን ምን ነገሮችን በሚያቀርቡት የዳኝነት ጥያቄ ውሥጥ አካተው ያቀርቡላታል?
    ለማጠቃለል
    በዋናነት የቤት ውስጥ ሰራተኞች የህግ ጥበቃ የሚያገኙት በሚያደርጉት ውል ነው / ውሉ በፅሁፍም ወይም ያለ ፅሁፍ ለደረጉ ይችላሉ፡፡ ሌላው የፍታብሄር ህጉ ስለቤት ሰራተኞች የሚደነግጋቸው አንቀፆች ናቸው፡፡የድንጋጌዎቹን አርእስ አዚጋ ማንሳት ህጉ እሚሰጠውን ጥበቃ ባከብርም ምን ያህል መሻሻል እሚያስፈልገው መሆኑን ያለ ተጨማሪ ማብራሪያ ገልፅልኛል፡፡‹‹ በቤተሰብ አስተዳደር ውስጥ ስለሚኖር አሽከር የስራ ውል›› በማለት ነውና ሚገልፀው፡፡/የፍ.ሕ.ቁ.2601-2604/ በተጨማሪነት የቤት ውስጥ ሠራተኞችን ( የግል ቅጥር አገልግሎት) የስራ ሁኔታን የሚመለከት ደንብ እንዲወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ህግ አውጪው ሃላፊነት ሰጥቶት ነበረ የሆነ ጊዜም የተወሰኑ እንቅሰቃሴዎች ተደርገው የተወሰኑ ዜሮ እረቂቆችን ማየቴን ባስታውስም አሁን ምን ላይ እንዳሉ መረጃው የለኝም፡፡/ መረጃው ያለው ቢያከፍለን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው/ ህጉን የማውጣቱ አስፈላጊነት ግን አሌ እሚባል አደለም፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃም የህጉን አሰፈላጊነት በማመን የቤት ውስጥ ሰራተኞች ኮንቬንሽን ቁትር 189 በአለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ተዘጋጅቶ ይገኛል፡፡
    በሚኩተሉት ማስፈንጠሪያዎችም ያገኙናል
    👇 👇 👇 👇 👇 👇
    በፌስ ቡክ ግሩፓችን – https://m.facebook.com/groups/1607340246185508/?ref=bookmarks
    በፌስ ቡክ ገፅ – https://m.facebook.com/Ethiopian-law-by-Daniel-Fikadu-law-office-510394779106487/?ref=bookmarks
    በዮትዩብ- https://m.youtube.com/channel/UCf8gaZ0CdpnHC8hTfFwvTOw
    በቴሌግራም – https://t.me/joinchat/AAAAAFR1urosOb6pOpoHmQ
    በድረገፅ -https://lawethiopiacomment.wordpress.co

Comments

Popular posts from this blog

የአጣሪ ዳኝነት ሚና በአስተዳደር ህግ

በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የሚቀርብ ክስን ማየት ስልጣን ያለው ማነው? በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)

ተወካይ የወካዩን እማይንቀሳቀስ ንብረት አስይዞ መበደር ስልጣን .... የሠ.መ.ቁ. 17320 / ቅፅ 5 / ላይ እና በመዝገቡ ላይ በኢትዮጵያ ጠበቆች የህግ መፅሄት መግዌ 5 ቁ.2 ላይ በተሰጠው ትችት ላይ የተሰጠ የትችት ትችት .....