የአጣሪ ዳኝነት ሚና በአስተዳደር ህግ
Ethiopian law by Daniel Fikadu Search SKIP TO CONTENT የአጣሪ ዳኝነት ምንነት እና ህገ መንግስታዊ ፋይዳውየአጣሪ ዳኝነት (Judicial Review) ትርጓሜ ከህገ መንግስት ወይም ከአስተዳደር ህግ አንጻር ሊቃኝ ይችላል፡፡ በህገ መንግስታዊነት ማዕቀፍ አጣሪ ዳኝነት ማለት በህግ አውጭው የሚወጡ ህጐች ህገ መንግስታዊ ባለመሆናቸው በመደበኛ ፍ/ቤት፣ በህገ መንግስታዊ ፍ/ቤት ወይም በሌላ ራሱን የቻለ ተቋም አማካይነት የሚሻሩበት ስርዓት ነው፡፡a በአስተዳደር ህግ ውስጥ አጣሪ ዳኝነት ማለት በህግ አስፈፃሚው ወይም በአስተዳደር መ/ቤቶች የሚወሰዱ ውሳኔዎች፣ የሚፈጸሙ ድርጊቶች እና በውክልና የሚወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ህጋዊነት በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚጣራበት ስርዓት ነው፡፡b ምንም እንኳን በህገ መንግስታዊነት እና በህጋዊነት መካከል ጥርት ያለ መለያ መስመር ማበጀት አዳጋች ቢሆንም የዚህ መጽሐፍ በተለይም የዚህ ምዕራፍ ወሰን ህገ መንግስታዊ አጣ...