Posts

Showing posts from July 3, 2022
10 መሰረታዊ የውል አተረጓጎም ደንቦች *** በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ እና የህግ አማካሪ) *** ውል ቅኔ መሆን የለበትም። በተቻለ መጠን ለሁሉም ተዋዋይ  ወገን እንዲሁም ለሶስተኛ ወገኖች ጭምር ግልፅ በሆነ መንገድ መደረግ አለበት ። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በተለያየ መንገድ የሚደረጉ ውሎች ግልፅነት የጎደላቸው ይሆኑና የግጭት ና ያለሙግባባት  መንስኤ ሆነው ለትርጉም አስማሚ ወይም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ይህ ሲሆን ፍርድ ቤቶች ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ መሰረታዊ የሆኑ የውል አተረጓጎም ደንቦች አሉ። እነሱን እጠር አርገን ከተያያዥ የሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉሞች ጋር  እንመልከት: የውል አተረጓጎም መሰረታዊ ደንቦች 1. ውሉ ግልፅ ከሆነ ምንም አይነት ትርጉም አያስፈልግም። ( If the contract is clear no need of interpretation ) /፩/ 2.  የውሉ ትርጉም ውጤት መገኘት ያለበት ከራሱ ከውሉ እንጂ ፣ ውሉ ወይም ግዴታው ከትርጉሙ ሂደት መመንጨት የለበትም። / The interpretation of the contract must come from the contract not the contract from the interpretation./  በሌላ አማርኛ ፍርድ ቤት ውልን በመተርጎም ስም ያልነበረ ውል ወይም ግዴታ ሊፈጥርና ሊሰራ አይችልም። 3. የቅን ልቦና አተረጓጎን ደንብ (1732)  :- ማንም ሰው የራሱን መብት በአግባቡ ከመጠቀም አልፎ በሌላው ተዋዋይ ላይ አላስፈላጊ ጉዳት የማድረስ ፍላጎት የለውም የሚል አወንታዊ  መነሻ ሃሳብ ( positive premise) አለ። ከዚህ ተቃራኒ የሄነ ሃስብ ይዞ ከቅን ልቦና በተቃራኒ ጉዳት ለማድረስ ያለው ተዋዋይ ወገን ካለ ህግ በመርህ ደረጃ ጥበቃ ያደርግለታል። /፪/ 4. በተገቢው መንገድ ያልተብራሩ ሃሳቦችን አተ