ተጠሪ
ተጠሪ * ዳንኤል ፍቃዱ / የህግ አማካሪና ጠበቃ/ * አንድ ተቋም ለአንድ ሌላ ተቋም ወይም ግለሰብ ተጠሪ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? ምን መብት ምን ግዴታስ በተጠሪው ላይ ይፈጥራል? በጠሪው ( ይጠራልህ በተባለው)ግለሰብ ወይም ተቋም ላይስ? ከህገ መንግስቱ አንስቶ መመሪያ ድረስ ያሉ ህጎች ላይ ይህች ቀላል እምትመስል ቃል በየቦታው ተዱላ እንመለከታታለን ። በእንግሊዝኛው በተለዋዋጭ Accountable ወይም Responsible በሚል ተገልፃ እናገናታለን። እውቁ የህግ መዝገበ ቃላት Blacks law Dictionaryንም ስንመለከት ቃላቱ በተለዋዋጭ / interchangeably/ አገልግሎት ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ ሲያጠይቅ: Accountable = Responsible በሚል ይተረጉመዋል። ስለዚህ ሃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ መልስ ሰጪነት ፣ ወዘተ ተብሎ ሊተረጎም ይችል ይሆናል። ለምሳሌ ያህል ፩/ የኢፌድሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 49 (3) ላይ " የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌደራሉ መንግስት ይሆናል። " ይላል። ምን ማለት ይሆን ?ሰበር በሠ/መ/ቁጥር 34665 ቅፅ 10 ላይ " የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ስራ የመከታተልና በበላይነት የመቆጣጠር ስልጣን ያለው እንደመሆኑ መጠን የስራና ከተማ ልማት ሚኒስትር ቤቶችን የሚመለከት ጉዳይ ለአዲስ አበባ ስራና ከተማ ልማት ቢሮ እንዲያስተላልፍ በተሰጠው ትዕዛዝ ( ጠቅላይ ሚኒስትሩ በደብዳቤ ባስተላለፉት ) መሰረት ስራውና ሰራተኞችን ለቢሮው አስተላልፏል ። " ይለናል ይህ ማለት እንግዲህ የከተማ መስተዳድሩ በሚያወጣቸው ህጎች እና በሚወስናቸው ውሳኔዎች ሁሉ የፌደራሉን ይሁንታ ማግኘት አለበት ማለት ነው? ፌደራሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር