Posts

Showing posts from March 28, 2021

የቤት ውሰጥ ሰራተኞች ህግ ??? በዳንኤል ፍቃዱ(ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)

Image
  የአሰሪና ሰራተኛ ህጉ አዋጅ ቁጥር1156/2011 በአኝቀፅ 3 ስር የህጉን ተፈፃሚነት ወሰን በሚደነግግበት ወቅት በግለፅ ካገለላቸው የቅጥር ግንኙነቶች ውሰጥ . የመንግስት ሰራተኞች(አንቀፅ 3/2/ሠ/ የሠበር መ.ቁ. 14414 ቅፅ 2 ይመልከቱ ) . የስራ መሪዎች ( አንቀፅ 3/2/ሐ/የሠበር መ.ቁ. 84661 ቅፅ 15 ፣የሠበር መ.ቁ. 92466 ቅፅ 15 ፣ የሠበር መ.ቁ. 11969 ቅፅ 20 ፣ እና ሌሎችንም የሰበር ውሳኔዎችን መመልከት ይቻላል) . የቤት ውሰጥ ሰራተኞች (አንቀፅ 3/2/መ/) ወዘተ…ሲገኙ በግልፅ ሳይሆን በቅድመ ሁኔታ የሚገለሉ የቅጥር ግንኙነቶችንም አስቀምጧል፡፡(አንቀፅ 3/3/)በዚህ አንቀፅ ላይ ህጉ አንዳንድ ለወደፊቱ ሊደረጉ የሚችሉ ነገሮችን ያስቀምጥናእነዛ ነገሮች ተሟልተው ሲገኙበተጠቀሱት የቅጥር ግንኙነቶች ላይ አዋጁ ተፈፃሚነት አይኖረውም ማለት ነው፡፡እነዛ ቅድመሁኔታዎች እሰካልተሟሉ ወይም እሰካልተፈፀሙ ድረስ ግን እነዚህ የቅጥር ግንኙነቶች የሚገዙት በአዋጁ መሰረት መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ገንኙነቶች ሁለት ሲሆኑ 1.በውጭ ኤምባሲዎች እና አለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሰሩ ሰራተኞች ( አንቀፅ 3/3/ሀ/) የሠበር መ.ቁ. 117390 ቅፅ 19፣ የሠበር መ.ቁ. 98541 ቅፅ 17 ይመለከቱ) 2.የሃይማኖት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሰራተኞች (አንቀፅ 3/3/ለ/) የሠበር መ.ቁ. 67996 ቅፅ 13፣የሠበር መ.ቁ. 50923 ቅፅ 9 ፣ የሠበር መ.ቁ. 98771 ቅፅ 20 ይመልከቱ) ለመነሻ ያክል የህን ካልኩ ለዛሬ የቤት ውሰጥ ሰራተኞችን ጉዳይ ላይ ትንሽ ልጨምር፤ የቤት ውሰጥ ሰራተኞች የሚባሉት በዋናነት የጓዳ ስራን የሚሰሩ፣ የሚያፀዱ ፣ምግብ የሚያዘጋጁ፣ ዘበኞችን እና አትክልተኞችን መጥቀስ ይቻላል፡፡እንደስራው ሁኔታ ሌሎችም ስ

በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የሚቀርብ ክስን ማየት ስልጣን ያለው ማነው? በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)

      በወታደራዊ አካሉ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ፣ የሃገር ክህደት ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ከፍተኛ መኮንኖች ላይ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የምርመራ መዝገብ መከፈቱን ተከትሎ ፣ እነዴት ወታደር በመደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ይታያል በሚል ስልጣን ጥያቄ እና በፍትህ ስርአቱ ላይ ትችት ሲሰነዘር ተመልክተናል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ ጠቅለል ባለ መልኩ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የሚቀርብ ክስን ማየት ስልጣን ያለው ማነው? የሚለውን ለመዳሰስ ተሞክሯል::       ፍርድ ቤቶች በህግ የሚቋቋሙ እንደመሆናቸው የዳኝነት ስልጣናቸው ከህግ ይመነጫል፡፡ በአንድ ፍርድ ቤት የቀረበ ጉዳይ የክስ ምክንያት አለው ብሎ ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሹ የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ህግ ይፈቅድለታል ወይ? የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት አወንታዊ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡       ከዚህ እንግዲ መረዳት የሚቻለው የማንኛውም ፍርድ ቤት ጉዳይን ተመልክቶ የመውሰን ስልጣን በህግ ተወስኖ የተሰጠ ወይም የሚሰጥ መሆኑን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ህግ ፍርድ ቤቶች ተፈጥሯዊ ስልጣን (Natural/inherent power) በህግ በሚታዩ ጉዳዮች (Justiciable matters) ላይ የላቸውም የሚለው ሃሳብ አከራካሪነቱ እንዳለ ቢሆንም በዙ ባለሙያዎች የሚስማሙበት ነው፡፡( በጉዳዩ ላይ ከዚህ ቀደም በቀድሞ ገፃች  https://m.facebook.com/groups/1607340246185508/?ref=bookmarks  ወይምhttps://m.facebook.com/Ethiopian-law-by-Daniel-Fikadu-law-office-510394779106487/?ref=bookmarks የፃፍከት ሰፋ ያለ ፅሁፍ ስላለ ፈልጋችሁ ተመልከቱት)ወታ