በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የሚቀርብ ክስን ማየት ስልጣን ያለው ማነው? በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)

 

    በወታደራዊ አካሉ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል ፣ የሃገር ክህደት ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ከፍተኛ መኮንኖች ላይ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የምርመራ መዝገብ መከፈቱን ተከትሎ ፣ እነዴት ወታደር በመደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ይታያል በሚል ስልጣን ጥያቄ እና በፍትህ ስርአቱ ላይ ትችት ሲሰነዘር ተመልክተናል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ ጠቅለል ባለ መልኩ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የሚቀርብ ክስን ማየት ስልጣን ያለው ማነው? የሚለውን ለመዳሰስ ተሞክሯል::
   

 ፍርድ ቤቶች በህግ የሚቋቋሙ እንደመሆናቸው የዳኝነት ስልጣናቸው ከህግ ይመነጫል፡፡ በአንድ ፍርድ ቤት የቀረበ ጉዳይ የክስ ምክንያት አለው ብሎ ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሹ የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ህግ ይፈቅድለታል ወይ? የሚለው ጥያቄ ሲነሳ ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት አወንታዊ ምላሽ መስጠት የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
   

 ከዚህ እንግዲ መረዳት የሚቻለው የማንኛውም ፍርድ ቤት ጉዳይን ተመልክቶ የመውሰን ስልጣን በህግ ተወስኖ የተሰጠ ወይም የሚሰጥ መሆኑን ነው፡፡ በኢትዮጵያ ህግ ፍርድ ቤቶች ተፈጥሯዊ ስልጣን (Natural/inherent power) በህግ በሚታዩ ጉዳዮች (Justiciable matters) ላይ የላቸውም የሚለው ሃሳብ አከራካሪነቱ እንዳለ ቢሆንም በዙ ባለሙያዎች የሚስማሙበት ነው፡፡( በጉዳዩ ላይ ከዚህ ቀደም በቀድሞ ገፃች https://m.facebook.com/groups/1607340246185508/?ref=bookmarks ወይምhttps://m.facebook.com/Ethiopian-law-by-Daniel-Fikadu-law-office-510394779106487/?ref=bookmarks የፃፍከት ሰፋ ያለ ፅሁፍ ስላለ ፈልጋችሁ ተመልከቱት)ወታደራዊ ፍርድ ቤቶችም እንደሌሎቹ ፍርድ ቤቶች በህግ የተቋቋሙ እና የዳኝነት ስልጣናቸውም በህግ ተሰፍሮ ተለክቶ የተሰጠ ነው፡፡ 

    በመሆኑም በወታደር ተፈፀመ የተባለ የወንጀል ድርጊት በመከላከያ ሰራዊት ውስት ተቀትሮ በውትድርና የሚያከናውነውን ተግባር ሲሰራ በነበረበት የተፈፀመ ከሆነ ክሱ የሚታየው በወታደራዊ ፍርድ ቤት ነው፡፡
በመከላከያ አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 1100/2011 አንቀፅ 28 (3) ስለወታደራዊ ፍትህ አካላት ሲዘረዝር በወታደራዊ ሰራዊት ውስጥ የወታደራዊ ፍትህ ስራን የሚያከናውኑ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች መቋቋማቸውን ይደነግጋል፡፡ እነዚህ ፍርድ ቤቶች በሁለት ደረጃ የተቋቋሙ ሲሆን አንደኛ ቀዳሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤት እና ሁለተኛ ደግሞ ይግባኝ ሰሚ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በመባል እንደሚጠሩ የአዋጁ አንቀፅ 37 (1) እና (2) በግልፅ ያመለክታል፡፡ በመሆኑም በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ውስጥ እነዚህ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች በህግ ተቋቁመው በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡
   

 እነዚህ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች የተፈፀመው ወንጀል በኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 28 መሰረት በስብዕና ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች፣ በወንጀል ህጉ ከአንቀፅ 284 – አንቀፅ 322 ከተዘረዘሩት ውስጥ (ዓለምዓቀፍ ህጎችን በመጣስ የሚፈፀሙ ወንጀሎች-ለምሳሌ ዘር ማጥፋት (Genocide)፣ በሰብዓዊ ድርጅቶች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እና ወታደራዊ ወንጀሎች) አንዱ ከሆነ ወይም በዓለምዓቀፍ ህግ (የዘር ማጥፋት፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ወዘተ) ወይም በወታደራዊ ተግባር ላይ ከሚደረጉት ወንጀሎች አንዱ ከሆነ የመከላከያ ሰራዊቱ አባል የሚዳኘው በኢፌዲሪ የወንጀል ህግና በኢትዮጵያ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የመከላከያ አዋጁ በማንኛውም የመከላከያ ሰራዊት አባል ላይ እንዲሁም እንደአግባብነቱ በሲቪሎችም ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

በመከሊከያ ሠራዊት ውስጥ የወታደራዊ ፍትህ ሥራን የሚያከናውኑ የሚከተለት አካሊት በአዋጁ ተቋቁመዋል፡-

1/ ወታደራዊ ፖሊስ፣
2/ ወታደራዊ ዓቃቢ ህግ፣
3/ ወታደራዊ ፍርድ ቤቶች፣ እና
4/ ወታደራዊ ተከሊካይ ጠበቃ፡፡ /// አዋጅ ቁጥር 1100/2011 አንቀፅ 2(14) ፣ 28 ///

አንቀፅ 38 – የወታደራዊ ፍርድ ቤት የዲኝነት ስልጣንን በተመለከተ የአዋጁ ከአንቀፅ 38-40 ድረስ የሚከተሉትን ስልጣናት ይደነግጋሉ፤

ሀ) በወንጀል ህጉ ከአንቀፅ 284 እስከ አንቀፅ 322 በተደነገጉት ወታደራዊ ወንጀልች ተጠያቂ በሚሆኑ ሰዎች፤
ለ) በሠራዊት አባላት መካከል በሚፈፀሙ የግድያ፣ የድብደባ እና የአካል ማጉደል ወንጀሎች፤
ሐ) ማንኛውም የሠራዊት አባሌ በአገር ውስጥ በጦር ሜዳ ግደጅ ላይ ሆኖ በሚፈጽማቸው ማናቸውም ወንጀሎች፤
መ) በውጭ አገር ግዳጅ ወይም በጦር ሜዳ ግዳጅ ከተሰማራ የጦር ክፍል ጋር የዘመተ የሠራዊት አባሌ ወይም ሲቪልች በሚፈፅሟቸው ማናቸውም ወንጀሎች፤
ሠ) በአገር ውስጥ የጦር ክተት አዋጅ በታወጀበት ወይም የጦር አደጋ ምልክት በተሰጠበት ጊዛ ከሠራዊቱ ጋር የዘመቱ ሲቪሎች፣ የመደበኛ ፖሊስ አባላት እና ሚሊሻዎች በሚፈጽሟቸው ማናቸውም ወንጀሎች፤
ረ) የጦር ምርኮኞች ከተማረኩ በኋላ በሚፈፅሟቸው ማናቸውም ወንጀልች፤

ሰ) ምልምል ወታደሮች ወደ ማሰለጠኛ ከገቡ በኋላ ወይም የብሔራዊ ተጠባባቂ ሃይለ አባላት ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ከገቡ ወይም ከመደበኛ ሠራዊት ጋር ከተቀላቀሉ በኋላ በሚፈጽሟቸው በወታደራዊ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን ሥር የሚወድቁ ወንጀሎች፤

ሸ) በውጊያ የተማረኩ ሰዎች የጦር ምርኮኞች መሆን አለመሆናቸዉን የመለየት ጉዳዮች፡፡

ንኡስ አንቀፅ 2/ አንድ ተከሳሽ ከቀረቡበት ክሶች መካከል ከፊሉ በወታደራዊ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣን ከፉሉ ደግሞ በመደበኛ ፍርድ ቤት የዳኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ከሆነ ሁሉም ክሶች ከባድ ቅጣት የሚያስከትለውን ወንጀል የማየት ስልጣን ወዳለው ፍርድ ቤት ተጠቃለው ይቀርባሉ፡፡

አንቀፅ 40 ደግሞ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበትን በወታደራዊ ፍርድ ቤት የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ በማረም በሰበር ችሎት የማየት ሥሌጣን አለው፡፡ ይላል፤
ስለዚህ በመነሻችን ላይ ለተነሳው ወቅታዊ ጉዳይ የአዋጁ አንቀፅ 38(2) ምላሽ ሊሆን የሚችልበት እድል ይኖራል፡፡በመሆኑም ማናኛውም ፍርድ ቤት በቀረበለት ጉዳይ ወይም ክስ ላይ በህግ የተሰጠ የዳኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት ፡፡ በህግ የተሰጠ የዳኝነት ስልጣን ስልጣን ሳኖር የሚሰጥ ውሳኔ የህግ መሰረት ያለው ነው ወይም ህጋዊ ውሳኔ ነው ለማለት አይቻልም፡፡
/የሰበር መዝገብ ቁጥር 33368( ቀፅ 9 ) ፣ ሠ/መ/ቁ 23608(ቅፅ 6)/

Comments

Popular posts from this blog

የአጣሪ ዳኝነት ሚና በአስተዳደር ህግ

ተወካይ የወካዩን እማይንቀሳቀስ ንብረት አስይዞ መበደር ስልጣን .... የሠ.መ.ቁ. 17320 / ቅፅ 5 / ላይ እና በመዝገቡ ላይ በኢትዮጵያ ጠበቆች የህግ መፅሄት መግዌ 5 ቁ.2 ላይ በተሰጠው ትችት ላይ የተሰጠ የትችት ትችት .....