ተወካይ የወካዩን እማይንቀሳቀስ ንብረት አስይዞ መበደር ስልጣን .... የሠ.መ.ቁ. 17320 / ቅፅ 5 / ላይ እና በመዝገቡ ላይ በኢትዮጵያ ጠበቆች የህግ መፅሄት መግዌ 5 ቁ.2 ላይ በተሰጠው ትችት ላይ የተሰጠ የትችት ትችት .....


ዳንኤል ፍቃዱ / በማንኛውም ፍ.ቤት ጠበቃ / 0913158507/

....

የሰበር ሰሚው ውሳኔ ባጭሩ

ተከራካሪዎች ከታች ፍ.ቤት ጀምሮ ሲከራከሩ የነበሩበት በቤት ላይ የተሰጡ 2 የተለያዩ  ልዩ ውክልናዎች  ሲሆን አንደኛው ውክልና ህጋዊነቱ አልተካደም ሁለተኛው ውክልና ግን የተጭበረበረ ስለመሆኑ ክርክር ቀርቦበታል / በወንጀል ህግ ቁ. 358(1) እሚያስጠይቅ ድርጊት ነው ~ በወንጀል ክስ ስለመቅረቡ የፓሊስ ምርመራ መዝገብ እንደነበር ከመዝገቡ መረዳት ይቻላል /  አከራካሪው ድርጊት ተወካይ የተጭበረበረውን ውክልና ተጠቅመው የወከሉዋቸውን ባልና ሚስት / የተጭበረበረ በተባለው ሁለተኛው ውክልና ላይ ተወካዮች ሁለቱ ሳይሆኑ አንዱ ብቻ ነው/ ንብረት አስይዘው ከባንክ ብድር ተበድረው ለግላቸው ተጠቅመውበታል ፤ ባንኩም ይህን የተጭበረበረ ሰነድ ሳያጣራ አበድሯል፣ በተጨማሪም "ሁለቱም " ውክልናዎች የመሸጥ የመለወጥ እና የማስተዳደርን ስልጣን ለተወካይ ይሰጣሉ እንጂ አስይዞ የመበደር ስልጣን አይሰጡትም የሚሉ ሲሆኑ ። ጉዳዩን የተመለከቱት የመጀመሪያው እና ከፍተኛው ፍ.ቤቶች ባንኩ የወካዮችን ቤት በመያዣነት በመያዝ ብድር የሰጠው በአግባቡ አይደለም በማለት የመያዣ ውሉን ፈራሽ በማድረግ የባለቤትነት ሰነዱን ለወካዮች ይመልስ ሲሉ ወስነዋል። ሰበር ሰሚው ይህን ውሳኔ በመቀልበስ 

1. ሁለተኛው ውክልና የተጭበረበረ ነው የሚለውን ብቻ በመመርመር የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው።

2. ሊታይ እሚገባው ሁለተኛው ውል ሳይሆን የመጀመሪያ /ህጋዊው/ ውል ነው ምክንያቱም እሱም ፀንቶ ባለበት ነው የማስያዣ ውሉ የተደረገው / ምንም እንኳን ባንኩ ጋር የተደረገው የመያዣ ውል በ2ተኛው የተጭበረበረ ውል ቢሆንም /

3. የመጀመሪያ ውል አስይዞ የመበደር ስልጣን ለተወካይ ባይሰጠውም የመሸጥ የመለወጥ መብት ስለሰጠው በፍ/ብ/ህ/ቁ 2206(1) እና 3049(2) መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ ችሎታ ያለው ለራሱ እዳ በዋስትናነት ሊያስይዘው ይችላል ስለሚል የውክልና ውሉን ህጋዊ ውጤት ሰቶታል።

....

ከላይ የተጠቀሰው የህግ መፅሄት ደግሞ ውክልና ጥልቅ በሆነ ቅን ልቦና ከራስ ጥቅም ይልቅ የወካይን ጥቅም በማስቀደም እሚሰራ ተግባር መሆኑን በሰፊው በማተት/ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2208 እና 2209(1) / የይዞታ ማረጋገጫ የሌለው / ተወካይም ቢሆን + በግልፅ ውክልናው ላይ ቢሰፍርም በሚመስል መልኩ / አሲዞ የመበደር ስልጣን የለውም በማለት የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1195 እና 1196(ለ)፣ 3051(1) ን በመጥቀስ ሰበር ሰሚው ራሱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ሰርቷል ይላል።

....

ሁለቱም አተያዮች ከነቀፋ ነፃ ሆነው አልታዩኝም 

1. የሰበር ሰሚው ሁለተኛውን የተጭበረበረ ውክልና እያየ እንዳላየ ማለፋ እና በመጀመሪያው ውክልና ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነት የለውም ። ከዛ ውጪ ግን ሁለተኛው ውል ባይኖር ሰበር ሰሚው የሰጠው ውሳኔ በተወሰነ መልኩ እሚያስማማ ቢሆንም የወካይን ሃሳብ ከግምት ውስጥ ግን ያስገባ አይደለም። ህጉም ትልቁን የመሸጥ ስልጣን ከሰጠህ አስይዞ መበደርንማ አትከለክልም እሚል ይመስላል።

2. የህግ መፅሄቱ የይዞታ ማረጋገጫ የሌለው / ተወካይም ቢሆን/ አስይዞ የመበደር ስልጣን የለውም በሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱ  ህጉን የውል ህግ መሰረታዊ ሃሳብን ፣ የውክልና ህግ መርህን እና ስለማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ እና ስለብወለድ አገድ የተገለፁትን የፍታብሄር ህጉን ክፍሎች ባግባቡ ያገናዘበ አይደለም።

3. የታች ፍ.ቤት እና ከፍተኛው ፍ.ቤት ሁለተኛው የውክልና ህግ የተጭበረበረ ነው በማለት ውጤት እንዳይኖረው ማድረጋቸው የተሻለ ህጋዊ ውሳኔ ነው።

Comments

Popular posts from this blog

የአጣሪ ዳኝነት ሚና በአስተዳደር ህግ

በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ የሚቀርብ ክስን ማየት ስልጣን ያለው ማነው? በዳንኤል ፍቃዱ ( ጠበቃ እና የህግ አማካሪ)