Posts

Showing posts from May 16, 2021

ተወካይ የወካዩን እማይንቀሳቀስ ንብረት አስይዞ መበደር ስልጣን .... የሠ.መ.ቁ. 17320 / ቅፅ 5 / ላይ እና በመዝገቡ ላይ በኢትዮጵያ ጠበቆች የህግ መፅሄት መግዌ 5 ቁ.2 ላይ በተሰጠው ትችት ላይ የተሰጠ የትችት ትችት .....

ዳንኤል ፍቃዱ / በማንኛውም ፍ.ቤት ጠበቃ / 0913158507/ .... የሰበር ሰሚው ውሳኔ ባጭሩ ተከራካሪዎች ከታች ፍ.ቤት ጀምሮ ሲከራከሩ የነበሩበት በቤት ላይ የተሰጡ 2 የተለያዩ  ልዩ ውክልናዎች  ሲሆን አንደኛው ውክልና ህጋዊነቱ አልተካደም ሁለተኛው ውክልና ግን የተጭበረበረ ስለመሆኑ ክርክር ቀርቦበታል / በወንጀል ህግ ቁ. 358(1) እሚያስጠይቅ ድርጊት ነው ~ በወንጀል ክስ ስለመቅረቡ የፓሊስ ምርመራ መዝገብ እንደነበር ከመዝገቡ መረዳት ይቻላል /  አከራካሪው ድርጊት ተወካይ የተጭበረበረውን ውክልና ተጠቅመው የወከሉዋቸውን ባልና ሚስት / የተጭበረበረ በተባለው ሁለተኛው ውክልና ላይ ተወካዮች ሁለቱ ሳይሆኑ አንዱ ብቻ ነው/ ንብረት አስይዘው ከባንክ ብድር ተበድረው ለግላቸው ተጠቅመውበታል ፤ ባንኩም ይህን የተጭበረበረ ሰነድ ሳያጣራ አበድሯል፣ በተጨማሪም "ሁለቱም " ውክልናዎች የመሸጥ የመለወጥ እና የማስተዳደርን ስልጣን ለተወካይ ይሰጣሉ እንጂ አስይዞ የመበደር ስልጣን አይሰጡትም የሚሉ ሲሆኑ ። ጉዳዩን የተመለከቱት የመጀመሪያው እና ከፍተኛው ፍ.ቤቶች ባንኩ የወካዮችን ቤት በመያዣነት በመያዝ ብድር የሰጠው በአግባቡ አይደለም በማለት የመያዣ ውሉን ፈራሽ በማድረግ የባለቤትነት ሰነዱን ለወካዮች ይመልስ ሲሉ ወስነዋል። ሰበር ሰሚው ይህን ውሳኔ በመቀልበስ  1. ሁለተኛው ውክልና የተጭበረበረ ነው የሚለውን ብቻ በመመርመር የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። 2. ሊታይ እሚገባው ሁለተኛው ውል ሳይሆን የመጀመሪያ /ህጋዊው/ ውል ነው ምክንያቱም እሱም ፀንቶ ባለበት ነው የማስያዣ ውሉ የተደረገው / ምንም እንኳን ባንኩ ጋር የተደረገው የመያዣ ውል በ2ተኛው የተጭበረበረ ውል ቢሆንም / 3. የመጀመሪያ ውል አስይዞ የመበደር ስልጣን